(1 Vote)

ፕላስቲክ ምርቶች በዕለት ተዕለት ህይወታችን ዙሪያ የከበቡን ነገሮች ናቸው፡፡ ፕላስቲክ ከውሃ መያዣዎቻችን አንስቶ ለልብስ መስሪያነት እሰከመዋል  ድረስ ደርሷል፡፡ የፕላስቲክ ምርት የዕለት ተዕለት ኑሮአችንን አቅልሏል ብለን ከምናስበው  በእጅጉ የበለጠ  ረቂቅ በሆነ መልኩ አካባቢያችንን በመበከልና የሥነምህዳርና የአየር ንብረት ለውጥን በማስከተል ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡

የፕላስቲክ ምርትና የአለማችን ሙቀት መጨመር መካከል ያለውን ትስስር በዚህ ጽሁፍ ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡
አብዛኛዎቹ የፕላስቲክ ምርቶች ከቅሬተ አካል (ፎሲል)፣ከተፈጥሮ ጋዝና ከነዳጅ የሚሰሩ በመሆናቸው ነዳጅን በማውጣት፣ በማጣራትና በማጓጓዝ ሂደት ላይ  እንደካርቦን ዳይኦክሳይድና ሜቴን የመሳሰሉ የግሪን ሃውስ ጋዞቸችን ወደከባቢ አየር በመልቀቅና በአየር ውስጥ ያለውን ሙቀት በመሰብሰብ የስነምህዳር ለውጥን ለማፋጠን ያላቸው አስተዋጽዖ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
የቅሬተ አካል (የፎሲል) ነዳጅን ወደፕላስቲክ ለመቀየር በጣም ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የግሪን ሃውስ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ይለቃል፡፡ ችግሩ በማምረት ሂደቱ ላይ ብቻ የሚበቃ ሳይሆን ቀጣይነትና ሰንሰለታዊ ተያያዥነት ያለው ችግር ያስከትላል፡፡
-      የቆሻሻ በአግባቡ አለመወገድ
የፕላስቲክ ቆሻሻዎች ክምር በአናሮቢክስ መንገድ ሲበጣጠሱ/ ሲሰባበሩ የሜታኔንን ልቀት ያባብሳሉ፡፡

-      የአካባቢ በፕላስቲክ ቆሻሻዎች መሞላት / መበከል
በሚሊዮኖች ቶን የሚገመቱ የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በየጊዜው ወደ ውሃ አላካላት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህም በውሃ አካላት ውስጥ ያለው ህይወት እና ከባቢያዊ ስነምህዳሩ ይበከላል፡፡ ከቆሻሻው የተወሰነው ወደ ማይክሮ ፕላስቲክነት በመቀየር በዑደት ( ሳይክል) ውሃ አካላት ውስጥ በሚኖሩ እንስሳት ሆድ ውስጥ በመግባት አልፎም  የሰውን ጤና ወደማወክ ይሸጋገራል፡፡

-      ዓለም አቀፍ ተግዳሮትና የጋራ ኃላፊነት
የአየር ንብረት ለውጥና የፕላስቲክ ምርት ቁርኝት በቀላሉ የማይታይ ፤መፍትሔውም ሩቅና  በቀላሉ የሚደረስበት ባለመሆኑ የመፍትሔ እርምጃዎቹ በግለሰብ፣ በንግድ/ ቢዝነስ ተቋማትና በፖሊሲ አውጪዎች በኩል ሊወሰዱ ይገባቸዋል፡፡

-      በግለሰብ ደረጃ
ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ከመጠቀም በተደጋጋሚ ልንጠቀምባቸው የሚችሉ ከጨርቅ የተሰሩ ከረጢቶችንና  የጠርሙስ ውሃ መያዣዎች የመሳሰሉትን በመጠቀም የፕላስቲክ ምርቶችን መጠቀምን መቀነስ/ ማስወገድ፡፡

-      በንግድ /ቢዝነስ ተቋማት
ለረጅም ጊዜ ሊያገለግሉ የሚችሉ ማሸጊያዎችን፣ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉና በቀላሉ ሊበሰብሱ የሚችሉ ማሸጊያዎችን መጠቀም፡፡

-    የፖሊሲ አውጪዎች
የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረትና መጠቀምን በእጅጉ መቀነስ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ለሚነድፉና ለሚተገብሩ የተለያዩ የማበረታቻና የድጋፍ ስልቶችን መንደፍ፡፡

ማጠቃለያ
ለቀጣዩ ትውልድ ሙቀታማነቱ የቀነሰ ዓለምን ለማቆየት የፕላስቲክ ምርት አጠቃቀማችን ላይ ስር ነቀል  ለውጥ ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ከፕላስቲክ ምርቶች ጋር ያለን ቁርኝት ባለበት መልኩ ሊቀጥል አይችልም፡፡ በፕላስቲክና በስነምህዳር ለውጥ መካከል ያለውን ትስስር በሚገባ በመገንዘብ አዲስ ስልት መንደፍ ይኖርብናል፡፡ የተሻለ የቆሻሻ አወጋገድና የፕላስቲክ ምርትን መቀነስ የሚያስችሉ እና የሚያግዙ የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታትና ኃላፊነት የሚሰማቸውን ተቋማት በመደገፍ ከፕላስቲክ ምርቶች በመላቀቅ ለወደፊቱ ትውልድ ከሙቀት መጨመር የተላቀቀች ዓለምን ማዘጋጀት እንችላለን፡፡
Eco-Justice Ethiopia
Environmental Protection Authority, FDRE
AACJ

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

Our Partners/ Affiliates