ራዕይ

ለስርዓተ ምህዳር፣ ለአካባቢና  የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ የሚረዱ ምቹ የሆኑ የዘላቂ ልማት ፖሊሲዎችና የህግ ማዕቀፎች እንዲወጡ፣ እንዲተገበሩና  ማህበረሰቡ ለከባቢያዊ ፍትህ ትኩረት እንዲሰጥ በማድረግ የበለጸገና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለቀጣዩ ትውልድ ማቆየት፡፡

ዓላማ

  • በአካባቢ ጥበቃና በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ህጎች በሚገባ እንዲተገበሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር  አብሮ መሥራት፡፡
  • በሃገሪቱ ባሉት ህጎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በማጥናት ለመፍትሄው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ መስራት፣
  • ዜጎች ንፁህና ጤናማነቱ የተረጋገጠ አካባቢ ላይ የመኖር ህገ-መንግስታዊ መብታቸው እንዲከበር፣ እንዲሁም መንግስትና ዜጎች አካባቢን ለመጠበቅ ያለባቸውን የህግ ግዴታ በአግባቡ እንዲተገብሩ ማገዝ፡፡
  • ኢትዮጵያ የአካባቢና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና እንክብካቤን በተመለከተ ጠቃሚ የሆኑ ዓለማቀፍ ህጎችንና ስምምነቶችን እንድትፈርምና ቀደም ሲልም የፈረመቻቸውንም  በአግባቡ እንዲተገብር ማገዝ፡፡
  • የአከባቢና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ጠቀሜታ ማህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያዳብር የተለያዩ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፡፡ የአከባቢና የስነ ምህዳር ሀብት እንክብካቤ ጠቀሜታና ይህ በማይተገበርበት ወቅት የሚያስከትለውን  ጉዳት በተመለከተ ከህትመትና ከኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎች ጋር በመተባበር ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማከናወን፡፡
  • የሥነ ምህዳር ህጎች በመጣሳቸው ምክንያት ጉዳት ለሚደርስባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች/ግለሰቦች በችግራቸው መድረስና ከችግራቸው መውጣትና መልሰው የሚggሙበትን መንገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ማመቻቸት፣
  • የአከባቢ፣ የተፈጥሮ ሀብትና ስነ ምህዳር ተቋማት፣ ክበባት እንዲቋቋሙ፣ እንዲጠናከሩ መቀስቀስና ማገዝ፤ በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ኢትዩጵያ ጥሩ የሆኑ የሥራ ግንኙነቶችን በመፍጠር የአከባቢና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ፡፡
More in this category: « CONTACT

Our Partners/ Affiliates